የአገና ፖሊ-ቴክኒክ ኮሌጅ በውስጥ አቅም ባመረታቸው የተለያዩ ቴክኖሎጂዎች ምርትና ምርታማነቱን ለማሳደግና የውስጥ ገቢ ለማዳበር በርካታ ጥረቶች እያደረገ ይገኛል። በተጨማሪም በኮሌጁ አሰልጣኞች የሚሰራው የገፅታ ግንባታ ስራ ዕቅድ አካል አንዱ የሆነውን ዋናው መግቢያ በር ግንባታ ተጀምሯል። በሌላ በኩል በተመጣጣኝ ዋጋ ዘመናዊ የንብ ቀፎ ከወረዳው እርሻ ተፈጥሮ ሃብት ጋር በመቀናጀት ለአርሶአደሩ እያቀረበ ሲሆን ለከተማው ወጣቶች ላይብረሪ የመጽሐፍት መደርደሪያ ሰርቶ በመስጠት የማህበረሰብ ተሳትፎ ግዴታውን ተወጥቷል። በኮሌጃችን ገብስ/ስንዴ ማጨጃ ማሽን በመሰብሰብ በራሳችን ገብስ/ስንዴ መውቂያ ማሽን(ቴክኖሎጂ ) ምርቱ የተሰበሰበው የእርሻ ስራ ሰፋ ባለመልኩ ቢሰራ ከፍተኛ ገቢ እንደሚገኝ በተግባር መማር የቻልንበት ተግባር ሆኗል። ኮሌጃችን ከማሰልጠን ባሻገር በቀጣይ የገቢ አማራጭ ማስፋትና ምቹ የስልጠና ቦታ መፍጠር ላይ ልዩ ትኩረት በመስጠት የሚሰራ ይሆናል ሲል የዘገበው የአገና ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የኮሚኒኬሽን ገጽ ነው!!





