ለሙያ ብቃት ማረጋገጫ ምዘና(COC) አገልግሎት ፈላጊዎች በሙሉ:-
የአገና ኮንስትራክሽንና ኢንደስትሪያል ኮሌጅ በ2016 በጀት ዓመት ለ5ኛ ዙር የሙያ ብቃት ምዘና አገልግሎት የምዝገባ ፕሮግራም ከግንቦት 05-13/2016 ድረስ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
ማሳሰቢያ:- በምዝገባ ወቅት መሟላት ያለባቸው መስፈርቶች በተመለከተ:-
#1. የዲግሪ/ዲፕሎማ ሰርተፊኬት ኮፒ
#2. ከደረጃ-1 በላይ ተመዛኞች ከምዘና ደረጃው በታች ያሉ የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ኮፒ
#3. ቀደም ሲል ለብቃት ምዘናው የተፈቀደ ክፍያ ብር ላይ 120 ብር በመጨመር(ምሳሌ HNS ክፍያ=270+120ብር) በንግድ ባንክ አካውንት ቁ. 1000168288248 የተከፈለበት ደረሰኝ በምዝገባ ወቅት ማሟላት ግዴታ ነው:
#4.ተመዛኞች በምዘና ወቅት የሚፈጠረውን መጨናነቅና የስራ ጫና ለማስወገድ ትክክለኛ የሆነ የግል ስልክ ቁጥራችሁን እና ስማችሁ በእንግሊዝኛ(capital letter) በመስጠት እንድትመዘገቡ።




