እጅግ በጣም አስቸኳይ

ለሙያ ብቃት ማረጋገጫ ምዘና(COC) አገልግሎት የተመዘገባችሁ በሙሉ
የአገና ኮንስትራክሽንና ኢንደስትሪያል ኮሌጅ የ1ኛ ዙር የሙያ ብቃት ምዘና አገልግሎት ከነሐሴ 6-7/2015 ከጠዋቱ 2:00 ሰዓት ጀምሮ ይሰጣል፡፡
✍️ማሳሰቢያ:-
በምዘናው ዕለት ተመዛኞች የሚከተሉትን ጉዳዮች በጥንቃቄ መፈጸም ይጠበቅባቸዋል:-

1. ከኮሌጁ የተሰጠ የፈተና አዳራሽ መግቢያ ስሊፕ
2. ማንነታችሁን በግልጽ የሚገልፅ የቀበሌ/የኮሌጁ መታወቂያ
3. አንድ 4X3 የሆነ ጉርድ ፎቶግራፍ መሉ ስምና የሙያ ዓይነትና ደረጃ የተጻፈበት
4. በዕለቱ ከጠዋቱ 2:00 ሰዓት የኮሌጁ ጊቢ ውስጥ  ተፈትሾ መግባት
5. ምንም ዓይነት ልብስ ወይም ሌሎች ቁሶች በቦርሳ ይዞ መግባት የተከለከለ ነው!!
6. ለሌሎች ተመዛኞች ተክቶ መመዘን:ሰነድ ማጭበርበር ወይም ሌላ ማንኛው የምዘና አሰራር መጣስ በወንጀል የሚያስቀጣ መሆኑን መረዳት እና ተገቢውን መመሪያ መተግበር ያስፈልጋል።

Recent