ጥቅምት 15/2018 ዓ.ም አገና ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ
*****
የአገና ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ባዘጋጀው የግንዛቤ መፍጠሪያና የሰልጣኝ ቅበላ ንቅናቄ መድረክ ላይ አጠቃላይ የእዣ ወረዳና የአገና ከተማ አስተዳደር የካቢኔ አባላት የተገኙ ሲሆን በመድረኩ “የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ነባራዊ ሁኔታ-የገጠሙን ችግሮችንና መፍትሄዎች” በሚል ርዕስ የኮሌጁ ዲን አቶ አስቻለው ስባኒ የግንዛቤ ሰነድና ለውይይት የሚሆኑ የአመራር አቅጣጫ በሚሹ ጉዳዮች ላይም መነሻ ሀሳብ አቅርበዋል። በመድረኩ የተገኙት አስተባባሪ አመራሮችና ሌሎች የካቢኔ አባላት ሰፊ ሀሳብ አንስተው ውይይት የተደረገ ሲሆን በዋናነት አጠቃላይ የወጣቶች የቀጣይ ዕጣፈንታ የሚወሰነው አሁን በሚያገኙት የክህሎት ስልጠና ላይ መሆኑን የአለምአቀፍና የሀገራችን የቀጣይ የዕድገት መሰረቶች ኢንደስትሪዎች መሆናቸው በመረዳት መሆኑን አበክረው አንስተዋል።በመሆኑም አጠቃላይ ከማዕከል ጀምሮ እስከ ታችኛው አመራር፤ ማህበረሰብና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት ከወትሮ በተለየ መልኩ ዘርፉን በመረዳትና የአካባቢው ማህበረሰብ የቀጣይ ጊዜያት ሁኔታቸዎች በመረዳት ማንኛውም ወጣት እንደየ ትምህርት ደረጃው ከአጫጭር ስልጠና ጀምሮ በመደበኛ ስልጠናዎች ቢያንስ የአንድ ሙያ ባለቤት እንዲሆን መስራት ያስፈልጋል ብለዋል። በሌላ በኩል ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት የተነሳው ሀሳብ የኮሌጁ የውስጥ ገቢ ማሳደግ ሲሆን ኮሌጁ በራሱ አቅዶ ከሚሰራቸው የገቢ ማስገኛ ስራዎች ባሻገር አመራሩ በፈርኒቸር ምርቶች፤ በኮንስትራክሽንና በኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ጥገና ላይ ከኮሌጁ ጋር በቅንጅት በመስራት ሀብትን የማዳንና የኮሌጁ ገቢ ማሳደግ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ በትኩረት መስራት የአመራሩ ድርሻ ሊሆን ይገባልም ብለዋል።የኮሌጁ ዲን አቶ አስቻለው ስባኒ ከቴክኖሎጂ ማሻሻልና ማላመድ፤ከስልጠና ዘርፎች ማስፋፋትና ከላይ በተጠቀሱት የገቢ ማስገኛ ስራዎች ከመሰመራት አንፃር ህጋዊነትና ተያያዥ ጉዳዮች አንፃር የተነሳላቸው ጥያቄዎች ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
በመድረኩ የአገና ከተማ ከንቲባ አቶ ሀብቴ ዘርጋ፤ የእዣ ወረዳ የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ሃላፊ አቶ አብድራህማን እንዲሁም የአገና ከተማ ዋና የመንግስት ተጠሪ አቶ ከልል ክብሩ የተገኙ ሲሆን በመጨረሻም በቀጣይ አንድ ሳምንት ውስጥ በእዣ ወረዳ ሁሉም የቀበሌ መዋቅሮችና የአገና ከተማ የመንደር ውይይት መድረኮች ላይ ሰፊ ቅስቀሳና ግንዛቤ በመፍጠር የሰልጣኝ ቅበላ ዕቅድ ማሳካት እንዲቻል አቅጣጫ የተቀመጠ ሲሆን ኮሌጁ ህጋዊ ኢንተርፕራይዝ አቋቁሞ በሚንቀሳቀስባቸው የንግድ ዘርፎች ላይ የኮሌጁ የውስጥ ገቢ አቅም ማሳደግ ላይ በሁለቱም መዋቅሮች ተጨማሪ ውይይቶች ተደርገው አመራጮች እንዲቀርቡ በማለት መድረኩ ተጠናቋል።
ለወቅታዊ መረጃዎች ድህረገፃችን https://www.agenacollege.edu.et ቴሌግራም ቻናላችን https://t.me/agenacollege2007 እንዲሁም
በፌስቡክ ገፃችን https://facebook.com/agenacollege2007











