ሐምሌ 18/2017 ዓ.ም አገና ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ
*****
የአገና ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የዝግጅት ምዕራፍ ተግባራት በተለያዩ ዘርፎች በተጠናከረ መልኩ እየተገበረ እንደሚገኝ አስታወቀ።ኮሌጁ ከሐምሌ 07/2017 ዓ.ም ጀምሮ የክረምት ወቅት የክህሎት ስልጠና በተለያየ የትምህርት ደረጃ ለሚገኙ ተማሪዎች በኮምፒዩተር፤ በኤሌክትሮኒክስ፤ በኢንስታሌሽንና በጋርመንት ሙያ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሰልጣኞች ተቀብሎ እያሰለጠነ ከመሆኑም ባሻጋር ከተለያዩ የመንግስት ትም/ቤቶች የተወጣጡ መምህራንም የዚህ ፕሮግራም ተጠቃሚ ሆነዋል።
በሌላ በኩል የጋበር በጎአድራጎት ድርጅት የተገዙ የእርሻ ትራክተሮች ላይ ኮሌጃችን ከእዣ ወረዳ አስተዳደርና ከጋበር በጎአድራጎት ድርጅት ጋር በመተባበር አራት(04) ስልጠና ያጠናቀቁ የኮሌጃችን ተመራቂ ሰልጣኞች የእርሻ ትራክተር ኦፕሬተር በኢትዮ-ኢንጅነሪንግ አዳማ የእርሻ መሳሪያዎች ማምረቻ ድርጅት ስልጠና በማሰልጠን በወረዳው መንግስት በኩል ስራ ዕድል የተፈጠረላቸው ሲሆን ለመሰረታዊ ጥገና አገልግሎት ሶስት(04) የኮሌጃችን አሰልጣኞች እና ሁለት(02) የግብርና ባለሙያዎች የዚህ ስልጠና ተጠቃሚ አድርጓል።
ኮሌጃችን የውስጥ ገቢ ለማጠናከር በዛሬው ዕለት ከላይ የተጠቀሰውን የእርሻ ትራክተር ኦፕሬተር ስልጠና በሰለጠኑና ስራ ዕድል በተፈጠረላቸው የኮሌጃችን ተመራቂዎች አማካኝነት 1.5ሄክታር መሬት በእርሻ ትራክተር በማሳረስ በስንዴ ዘር እንዲሸፈን ተደርጓል። ከዚህ ጋር ተያይዞ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የቡናና የአቮካዶ ችግኞችን ከግል ባለሀብትና ከእዣ ወረዳ አስተዳደር ግብርና ፅ/ቤት በመቀበል ለተከታታይ ቀናት እየተተከለ ይገኛል።
ኮሌጃችን የክረምት የበጎ-አድራጎት ተግባራትና ሌሎች ስራዎችን ለማከናወን የሚያስፈልገውን በጀት በማኔጅመንት ደረጃ በመመደብና ማስፈፀሚያ ዕቅድ በማዘጋጀት ወደ ሙሉ ትግበራ የገባ ሲሆን አፈፃፀሙን በተከታታይ ለማህበረሰባችን የምናድርስ ይሆናል ሲሉ የኮሌጁ ዲን ገልፀዋል።
በመጨረሻም በኮሌጃችን የክረምት ክህሎት ስልጠና መሰልጠን ለምትፈልጉ የአገና ከተማ እና የእዣ ወረዳ አስተዳደር ውስጥ የምትገኙ መምህራንና ተማሪዎች ሰኞ ሐምሌ 21/2017 ዓ.ም ብቻ ለመጨረሻ ጊዜ መመዝገብና መሰልጠን የምትችሉ መሆኑን በዚሁ አጋጣሚ ኮሌጁ ጥሪውን ያቀርባል ሲል የዘገበው የኮሌጁ ድህረገፅ ነው።
ተከታታይ መረጃ እንዲደርሶ በኮሌጁ ድህረገፅ www.agenacollege.edu.et
እንዲሁም በቴሌግራም አድራሻችን https://t.me/agenacollege2007 ይጎብኙን!!














