የጋበር በጎ-አድራጎት ድርጅት አባል የሆኑት አቶ ሀብቴ ፈርሻ ለአገና ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የጋርመንት ስልጠና ክፍል ማሽነሪ ድጋፍ ስለማበርከት

አስደሳች ዜና
✍️ሚያዝያ 13/2017 ዓ.ም
የጋበር በጎ-አድራጎት ድርጅት አባል የሆኑት አቶ ሀብቴ ፈርሻ ለአገና ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የጋርመንት ስልጠና ክፍል ማሽነሪ ድጋፍ አበርክተዋል!!
አጠቃላይ የእዣ ወረዳ ተወላጅ ባለሀብቶች በጋበር በጎ-አድራጎት ድርጅት የቦርድ አመራሮች አስተባባሪነት ከ15ቀን (መጋቢት 27/2017) በፊት ኮሌጃችንን እንዲጎበኙ መደረጉ ይታወሳል። በጉብኝቱ ወቅት እያንዳንዱ ስልጠና ክፍል ተዘዋውሮ በመመልከት ያሉት አቅሞችንና የጎደሉት ማሽነሪዎች ገለጻ የተደረገ ሲሆን አብዛኛው ተሳታፊ ተወላጆች አቅማቸውን የፈቀደው ድጋፍ ለማድረግ ቃል በመግባት ወደ ተግባር የተገባ ሲሆን የመጀመሪያው ታሪካዊ ድጋፍ በበጎ አድራጎት ድርጅቱ አባል አቶ ሀብቴ 1.7ሚሊዮን ብር ወጪ የተደረገባቸው GEMSY industrial sewing machines ድጋፍ ተረክበናል። እንደዚህ ዓይት የግብዓት ድጋፎች እንዲቀጥሉና ሰልጣኞቻችን በዘመናዊ ማሽነሪዎች እንዲሰለጥኑ በማድረግ ትውልድ ተሻጋሪ አሻራ እንድታስቀምጡ ጥሪያችንን እያቀረብን ለዚህ ቅንነት የተሞላበት ድጋፍ በኮሌጁ ማህበረሰብ ስም ጋበር በጎአድራጎት ድርጅትንና አቶ ሀብቴ ፈርሻ ከልብ እናመሰግናለን!!

Recent