ታህሳስ 03/2018 ዓ.ም አገና ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ
*****
እጅግ ተስፋ ከጣልኩባቸው ስራ ፈጣሪ ወጣቶች መካከል አንዱ የሆነው የአገናፓሊ-ቴክኒክ ያፈራችው ጠንካራው ባለራዕይ !!
ወጣት ጌታሁን አመርጋ ይባላል በጉራጌ ዞን እዣ ወረዳ አገና ከተማ በጥቃቅንና አነስተኛ ዘርፍ በመሰማራት የቤትና የቤት እቃዎች ማምረቻ ድርጅት ከፍቶ ከራሱ አልፎ ለሌሎችም ጭምር ስራ ፈጥሯል ።
ጌታሁን ከዚህ በተጨማሪ ሌሎችም ሙያዎች ባለቤት ነው። ዘመኑን የሚጠይቅ ቤት ካስፈለገ በአጭር ግዜ ወለም ዘለም ያላለ የሚያምር ቤት ሰርቶ ያስረክቦታል ። ማንኛውም በብረታ ብረት ሚሰሩ ስራዎች እጅግ በዘመነ መልኩ ልክክ ያሉ ስራዎችን ይሰራል።
ወጣት ጌታቸው በአሁን ሰዓት ከራሱ አልፎ ለ6 ወጣቶች በቋሚነት የስራ እድል ፈጥሯል። ትህትና ፡ ሰው አክባሪነት፡ ጥንካሬ ፡ በቃሉ የሚገኝ ሰው ከተባለ የጌታሁን መገለጫ ናቸው ። ወጣቱ ሌት ተቀን ስራ ላይ ነው ምታገኙ የሚባክን ግዜ ለሱ ተረት ነው። በማንኛውም ማህበራዊና ሌሎችም ድጋፍ ሚያስፈልጉ ጉዳዮች ላይ እሱ ፊት ለፊት ተሳታፊ ነው ።
በነገራችን ላይ በርካታ ወጣቶች በአገና ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በተለያዩ የሙያ ዘርፎች ተምረው የራሳቸው ስራ በመፍጠር እና በተቋማት ተቀጥረው ውጤታማ ሆነዋል (እሱን በቅርቡ አጭር ዶክመንተሪ ይኖረናል ይጠብቁን )። ጌታሁንም የዚሁ ፍሬ ነው እንደዚህ አይነት ወጣቶች ይበራከቱልን!
ወጣት ጌታሁን ጋር በጥራትና በጊዜ ማሰራት የሚፈልግ 0912714648 አልያም በሳፊሪ ኮም 0718466239 ይደውሉ !!
©ደስታ ግዝያቱ
ለወቅታዊ መረጃዎች ድህረገፃችን https://www.agenacollege.edu.et ቴሌግራም ቻናላችን https://t.me/agenacollege2007 እንዲሁም
በፌስቡክ ገፃችን https://facebook.com/agenacollege2007









