የአገና ኮንስትራክሽንና ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ የተለያዩ  የቴክኖሎጂ  ምርቶች አምርቶ ለሽያጭ ማቅረቡን አስታወቀ

የአገና ኮንስትራክሽንና ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ የተለያዩ  የቴክኖሎጂ  ምርቶች አምርቶ ለሽያጭ ማቅረቡን አስታወቀ  ።

 እንደሚታወቀው ኮሌጁ የማህበረሰብ ችግር ፈቺ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን በማምረትና  በማስተዋወቅ እንዲሁም  በተግባር የሰለጠነ አምራች  የሰው ሀይል በማፍራት እጅግ አኩሪ የሆኑ ተግባራቶች እየፈፀመ ይገኛል።

የአገና ኮንስትራክሽንና ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ በሚያከናወናቸው አዳዲስ ተግባራቶች ለተከታታይ አመታት በተለያዩ ዘርፎች ግንባር ቀደም ሆኖ በዞኑ ብሎም በክልሉ እውቅና እያገኘም ይገኛል  ።

ለዚህም ትልቁ ስኬት በእውቀትና በቁርጠኝነት የተመራ የአመራር  ስልትና ትጉህና እውቀቱን ለማሳደግ ዝግጁ የሆነ እንዲሁም  ለማህበሩ ተቆርቋሪ ሰራተኛ ቅንጅታዊ አሰራር መኖሩን ተከትሎ መሆኑ በተለያየ ጊዜ በዘገብናቸው ዘገባዎች ላይ ለመገንዘብ ችለናል።

ኮሌጁ በቅርቡ  በኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽንና ቴክኖሎጂ ሽግግር እንዲሁም በአጫጭር ስልጠና ተግባራት ከአጠቃላይ የጉራጌ ዞን ኮሌጆች መካከል 1ኛ ደረጃ በመያዝ ተልዕኮውን በአግባቡ እየተወጣ እንደሚገኝ ተረጋግጧል ። 

በአሁን ሰዓትም ኮሌጁ የተለያዩ የቴክኖሎጂ ውጤት የሆኑና ለአካባቢው ማህበረሰብ  ጠቀሜታቸውን የጎላ የቴክኖሎጂ ውጤቶች አምርቶ ለሽያጭ  አቅርቦአል ። 

በኮሌጁ የአገና ኮንስትራክሽንና ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ ጠቅላላ የምርቶ አገልግሎት ማምረቻና  መስጫ የኢንተርፕራይዝ ማህበር ተመስርቶ ምርቱን የሚፈልጉ አካል መግዛት የሚችል ሲሆን ከተመረቱና ለሽያጭ ከቀረቡ ምርቶች መካከል :- 

ተንቀሳቃሽ የዶሮ ቤት ፡ ተደራራቢ አልጋ ፡ የከተማ ቆሻሻ ማስወገጃ ጋሪ ፡ እህል መውቂያ ማሽን ፡ በሞተር ሀይል የሚንቀሳቀስ ማረሻና መስመር ማውጫ ማሽን ፡ ገብስ ማጨጃ እንዲሁም ደረቅ ቆሻሻ መጣያ  ይገኙበታል ።

በአጠቃላይ በኮሌጁ እየተከናወኑ የሚገኙ እጅግ አበረታች ስራዎች ተጠናክሮ ይቀጥል እያልን ምርቶቹን የሚፈልግ ኮሌጁን ማነጋገር የሚቻል መሆኑን በአክብሮት አናሳውቃለን።

Recent