ከአጠቃላይ የጉራጌ ዞን ኮሌጆች መካከል 👉1ኛ ደረጃ🏆🏅

የአገና ኮንስትራክሽንና ኢንደስትሪያል ኮሌጅ በኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽንና ቴክኖሎጂ ሽግግር እንዲሁም በአጫጭር ስልጠና ተግባራት ከአጠቃላይ የጉራጌ ዞን ኮሌጆች መካከል 👉1ኛ ደረጃ🏆🏅በመያዝ ተልዕኮውን በአግባቡ እየተወጣ እንደሚገኝ ተረጋግጧል።
ኮሌጃችን ለኢንተርፕራይዝ አንቀሳቃሾች በሚሰጠው የጥራትና ምርታማነት ማሻሻያ: የንግድ ስራ አመራርና የሙያ ክህሎት ማሻሻያ ስልጠናዎች አማካኝነት እየጨመረ ያለው የምርት ጥራት መጨመርና የበርካታ ተጓዳኝ ቢዝነሶች መስፋፋት ጥሩ ማሳያዎች ቢሆንም የግብርና ዘርፉን በተለይም በዶሮ እርባታ: በወተት ምርት: በንብ እርባታ….ወዘተ ማህበራት ከመደገፍ ጋር የተለያዩ ቴክኖሎጂዎች ተዘጋጅተው ለአብዢ ኢንተርፕራይዞች እየተሸጋገሩ ከመሆኑም በሻገር በልዩ ዕቅድ እየተመራ መሆኑ ተገልጿል።
ኮሌጁ ከዞኑ ቴክኒክና ሙያ ትም/ስልጠና መምሪያ: አገና ከተማና ከእዣ ወረዳ አስተዳደር ስር ከሚገኙ የዘርፉ አመራሮችና ባለሙያዎች: ከወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ እና ከወልቂጤ ፖሊ-ቴክኒክ ኮሌጅ ጋር ባለው ጠንካራ የስራ ቅንጅት እየመጣ ያለውን ለውጥና በቀጣይ ከጥራት ጋር ተያይዞ መሰራት ስለሚገባቸው ጉዳዮች ከቦርድ አመራሮች ጋር በመገምገም አቅጣጫ ማስቀመጡና የተሻለ አፈጻጸም ያስመዘገቡ አሰልጣኞችና አስተዳደር ሰራተኞች ዕውቅና መስጠቱ ይታወሳል።
በመሆኑም የኮሌጃችን አሰልጣኞችና ማኔጅመንት አባላት እንኳን ደስ አላችሁ እያልን የተገኙ ውጤቶችና ተሞክሮዎችን በማስቀጠል የተጣለብንን ሀገራዊ ተልዕኮዎችን በጥራትና በፍጥነት በመፈጸም የኮሌጁ የማሰልጠን አቅም ወደ ደረጃ-5(ፖሊ-ቴክኒክ ኮሌጅነት ደረጃ) በማሳደግ የህብረተሰባችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ እንደሚጠበቅብን በዚሁ አጋጣሚ እንገልጻለን🙏🙏
ዘገባው:- የአገና ኮንስትራክሽንና ኢንደስትሪያል ኮሌጅ ነው::


Recent