እንኳን ደስ አላችሁ እንኳን ደስ አለን

⭐️⭐️⭐️እንኳን ደስ አላችሁ እንኳን ደስ አለን🙏🙏
በመጀመሪያ በሁሉም ነገር የረዳንን እግዚአብሔር አምላክ የተመሰገነ ይሁንና ታላቁን ሐገራዊ ሃላፊነት የተሰጠን ቢሆንም ለመወጣት ዝግጁ መሆናችን በተግባር የምናሳይበት ወሳኝ ምዕራፍ ተሸጋግረናል!!
በማዕከለዊ ኢትዮጵያ ክልል ቴክኒክና ሙያ ትምህርት ስልጠና ቢሮ ስር ከሚገኙ ኮንስትራክሽንና ኢንደስትሪያል ኮሌጆች መካከል በመወዳደር ደረጃውን አሟልቶ በመገኘት ከአገና ኮንስትራክሽንና ኢንደስትሪያል ኮሌጅነት ወደ ⭐️⭐️አገና ፖሊ-ቴክኒክ ኮሌጅ ዛሬ ተሸጋግረናል🙏🙏
ለሁሉም ባለድርሻ አካላት በተለይም ለጉራጌ ዞን አስተዳደርና የቴክኒክና ሙያ ት/ት ስልጠና መምሪያ: የእዣ ወረዳ እና አገና ከተማ አስተዳደር: ለወልቂጤ ፖሊ-ቴክኒክ ኮሌጅ እና ለክልሉ ቴክኒክና ሙያ ት/ት ስልጠና ቢሮ ማኔጅመንት አካላት ከምንም በላይ ደሞ ለዚህ ውጤት እዲበቃ ከልብ ሲደክሙ የነበሩት የኮሌጁ ዲን አቶ አስቻለው ስባኒ እና የማሌጅመንት አባላቶቻቸው ለሰሩት ታላቅ ስራ ከልብ እናመሰግናለን!!

የአገና ፖሊ-ቴክኒክ ኮሌጅ እንደተለመደው ሃገራዊ ራዕይና ተልዕኮን እያሳካ ወደፊት መጓዙብ ይቀጥላል።

⭐️⭐️⭐️ ለአረጓዴ ኢንዱስትሪ ፈጠራ እንተጋለን! ⭐️⭐️⭐️

የአገና ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ

Recent