የአገና ኮንስትራክሽንና ኢንደስትሪያል ኮሌጅ በ2016 በጀት ዓመት ለ2ኛ ዙር የሙያ ብቃት ምዘና አገልግሎት የምዝገባ ፕሮግራም ከነሀሴ 15-24/2015 ድረስ መመዝገብ ትችላላችሁ።በመሆኑም የምዘና አገልግሎት ለማግኘት መመዝገብ የምትፈልጉ አጫጭር ስልጠና ሰልጣኞች/የግል ተመዛኞች በሙሉ የሚከተሉትን መረጃዎች በሟሟላት መቅረብ ይጠበቅባችኋል:-
1. የዲግሪ/ዲፕሎማ ሰርተፊኬት ኮፒ
2. ማንነታችሁ የሚገልጽ የታደሰ መታወቂያ እና ሁለት/2/ ጉርድ ፎቶ-ግራፍ
3. ከደረጃ-1 በላይ ተመዛኞች ከምዘና ደረጃው በታች ያሉ የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ኮፒ
4. ለብቃት ምዘናው የተፈቀደ ክፍያ ብር በንግድ ባንክ አካውንት ቁ. 1000168288248 የተከፈለበት ደረሰኝ በምዝገባ ወቅት ማሟላት ግዴታ ነው።
✍️ማሳሰቢያ:- #1. ለአካውንቲንግ፣ ለማኔጅመንት እና ለHNS/Database ተመዛኞች ብቁ እንድትሆኑ(ምዘናውን እንድታልፉ) የሚያግዙ የተለያዩ ፈተናዎችንና መልመጃዎች ከምዘና ፕሮግራም ሶስት ቀናት አስቀድሞ በነጻ ክለሳ የሚሰጥ መሆኑን ከወዲሁ እንገልጻለን፡፡





